የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከሙሳ ፋኪ መሃማት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

February 13, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት አባል እና መቀመጫ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ለህብረቱ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምጥቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ሙሳ ፋኪ መሃማት በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በአፍሪካ ፀጥታ እና መረጋጋትን ለማስፈን ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

አምባሳደር ታዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሆነው በመሾማቸው ‘እንኳን ደስ አለዎት’ ያሉት ሙሳ ፋኪ መሃማት፤ የስራ ጊዜያቸው የተሳካ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልፀውላቸዋል፡፡