የሀገር ውስጥ ዜና

ከፍተኛ አመራሮች ሕዝባዊ ውይይቶችን ለመምራት ሐዋሳ ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

February 14, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ ነገ የሚካሄደውን ሕዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት ሐዋሳ ገብተዋል፡፡

አመራሮቹ ሐዋሳ ሲገቡ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡