አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በነገው ዕለት “ኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሐሳብ በ20 ከተሞች ሕዝባዊ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡
በአፋር ክልል የሚካሄደውን ሕዝባዊ ውይይት ለመምራትም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ሠመራ ገብተዋል፡፡
አመራሮቹ በሠመራ ሱልጣን አሊ ሚራሕ ሀንፍሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
በክልሉ በሠመራ እና አሳዒታ ከተሞች ሕዝባዊ የውይይት መድረኮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡
በታሪኩ ወ/ሰንበት
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!