አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የቦትስዋና፣ የኮትዲቯር፣ የላይቤሪያ እና የቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በ44ኛው የአስፈፃሚዎች ስብሰባ ላይ ለመካፈል ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሞጋንግ ክዋፔ (ዶ/ር) እና የኮትዲቯር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዶም ካኩ አዲስ አበባ መግባታቸው ተመላክቷል፡፡
እንዲሁም የላይቤሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳራ ቤይሶሎ ያንቲ እና የቤኒን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውሪሊየን አግቤኖንቺ አዲስ አበባ ገብተዋል፡