አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ህዝባዊ ውይይት የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በሐዋሳ ከተማ በተካሄደው ውይይት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር፣ ኢ/ር)፣ የሲዳማ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና የክልሉ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ሀብት የመፍጠር ጉዞዎች፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ መኩሪያ መርሻዬ ፥ ከተማዋ ብዙ እድሎች ያሏት ቢሆንም ተግዳሮቶችም ሲገጥማት እንደነበር ጠቅሰው፤ የመንገድ ልማትን ጨምሮ የመሰረተ ልማት ስራዎችን መተግበር፣ ከህዝቡ ጋር በቀጥታ በየሳምንቱ የመወያየትና የመፍታት አካሄዶች በመከተል ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል።
ስራ አጥነት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራሮች፣ በከተማ ውስጥ ሕገ ወጥ ተግባራት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደነበሩ ገልጸው፤ ችግሩን በግልፅ ከህዝቡ ጋር በመነጋገርና በመፈተሽ የማስተካከያ ስራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡
በሕገወጥ ተይዘው የነበሩ 806 ኮንቴነሮችና ሼዶችን በመቀበል ለታለመለት አላማ እንዲውል ተደርጓልም ብለዋል።
የልማት ስራዎችን ማስቀጠል፣ የስራ እድልን ማሳደግ፣ የገቢ አፈፃፀምን ማላቅ፣ የከተማዋን ሰላም መጠበቅ ላይ አበረታች ስራዎች እንደተሰሩም ተናግረዋል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!