አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ህዝባዊ ውይይት በዛሬው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ-ሎጊያ እና አሳዒታ ከተሞች ተካሄደ።
በክልሉ ሰመራ ከተማ የሚካሄደውን የውይይት መድረክ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ታንኳይ ጆክ፣ እንዲሁም የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዔላማ አቡበከር መርተውታል።
በውይይቱ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ ኢንቨስተሮች፣ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በተመሳሳይ አይሳኢታ ከተማ ላይ በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሴ አደን እንዲሁም የክልል ከፍተኛ የአመራር አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።
በታሪኩ ወ/ሰንበት
#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!