የሀገር ውስጥ ዜና

ከሕዝባዊ ውይይቶች የሚነሱ ሃሳቦች የመንግስት የቀጣይ እቅድ አካል ይሆናሉ – አቶ አረጋ ከበደ

By Melaku Gedif

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሕዝባዊ ውይይቶች የሚነሱ ሃሳቦች የመንግስት የቀጣይ እቅድ አካል ይሆናሉ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ፡፡

“ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሠላም እና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ሃሳብ በወልቂጤ ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት÷ በውይይት መድረኮች የሚነሱ የሕዝብ ሀሳቦችን ወስደን የቀጣይ እቅድ አካል በማድረግ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል።

የሀገሪቱና የአካባቢው አጠቃላይ የሰላም፣ የልማት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ያለበት ሁኔታ ላይ ውይይት እንደተደረገ መናገራቸውንም የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡