የሀገር ውስጥ ዜና

ለአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀመሩ

By Melaku Gedif

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፊታችን ቅዳሜ እና እሑድ ለሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡

በዚህ መሰረትም የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት በ37ኛ የአፍሪካ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዷለም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ አቀባበል አድርገውላቸዋል።