አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) ተወካይ ሳሙኤል ባይድ ዶው ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በአየር ንብረት ለውጥ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ በርካታ ሃብቶችን ማሰባሰብ እና መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
የተጀመረውን የኢትዮጵያ ስታስቲክስ ልማት ፕሮግራም ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በተለይ በዘላቂ የልማት ግቦች ላይ ቴክኒካል ድጋፍ እንደሚያደርግ ተወካዩ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል፡፡