የሀገር ውስጥ ዜና

ለትግራይ ክልል 16 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ኮንቴይነሮች ድጋፍ ተደረጉ

By Shambel Mihret

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ለወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የ16 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ኮንቴይነሮችን ለትግራይ ክልል ድጋፍ አድርጓል፡፡

የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ድጋፉን በመቀሌ ከተማ ተገኝተው ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስረክበዋል፡፡

በድርጅቱ የደረቅ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ምሕረተአብ ተክሉ ÷ ድጋፉ ወጣቱን ወደ ሥራ በማስገባት የልማት ተሳታፊ እንዲሆን ያስችለዋል ብለዋል፡፡

ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የክልሉ ቴክኒክና ሙያ እና የስራ እድል ፈጠራ ቢሮ ም/ሃላፊ አቶ ገብረመድህን ሓጎስ ናቸው።

ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ድጋፉ ወጣቶችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡