የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ኖርዌይ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

By Meseret Awoke

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከኖርዌይ የዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ሚኒስትር አኔ ቤዝ ቲቭነሪም ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት ፥ በአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ በደን ልማት፣በትምህርት ፣ በግብርና ዘርፍ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል።

አምባሳደር ታዬ በዚህ ወቅት ፥ ኖርዌይ በሁኔታዎች የማትቀየር የኢትዮጵያ ጠንካራ ወዳጅ ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

ሚኒስትር አኔ ቤዝ ቲቭነሪም በበኩላቸው ፥ ኖርዌይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቆየ ጠንካራ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ም ነው የተናገሩት፡፡

ሚኒስትሮቹ ሁለቱ ሀገራት በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!