የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራረሙ

By Meseret Awoke

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የስትራቴጂያዊ አጋርነት ስምምነት ተፈራርመዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የደቡብ አፍሪካ አቻቸው ናሌዲ ፓንዶር ስምምነቱን ዛሬ ከ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደ ስነ ስርዓት ላይ ፈርመዋል።

ስትራቴጂያዊ አጋርነቱ በፀረ-አፓርታይድ ትግል ወቅት የተፈጠረውን ጠንካራ ወዳጅነት መሰረት ያደረገ እና ፖለቲካዊ ትብብርን ለማሳደግ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን ለማስፋት ያለመ እንደሆነም ነው የተገለጸው።

ስምምነቱ በተለያዩ መስኮች ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነውም ተብሏል።

በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ በጋራ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ትብብር ማድረግ ከስምምነቱ ዋና ዓላማዎች አንዱ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia #SouthAfrica

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!