የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ

By Meseret Awoke

February 15, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አኪንዉሚ አዴሲና (ዶ/ር) ለ37ተኛው የአፍሪካ ኀብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።

ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱአለም አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡