የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አህመድ ሽዴ ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

February 16, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ ከኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ሙሀመድ አል ጃሰር (ዶ/ር) ጋር በኢኮኖሚ ልማት ዙሪያ ተወያይተዋል

በውይይቱ  አቶ አህመድ ኢትየጵያ የተለያዩ ፈተናዎችን ተቋቁማ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦችን እያስመዘገበች መሆኗን ገልፀዋል፡፡

ኢትየጵያ በአፍሪካ ቀንድ ኢኒሺየቲቭ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች መሆኗን ያነሱት ሚኒስትሩ÷ የኢስላሚክ ልማት ባንክም የኢኒሺየቲቩ አባል እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢስላሚክ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንቱ  በበኩላቸው÷ ባንኩ በኢትዮጰያ 44 ፕሮጀክቶችን በገንዘብ እየደገፈ እንደሚገኝ አንስተው÷ ለኢትየጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱም መጨረሻ ለሰብአዊ አገልግሎት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ፊርማ መከናወኑን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡