የሀገር ውስጥ ዜና

በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ያለው ኢ-ፍትሃዊ አሰራር አስቸኳይ መፍትሄን ይሻል – የብራዚል ፕሬዚዳንት

By Meseret Awoke

February 17, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ያለው ኢ-ፍትሃዊ አሰራር አስቸኳይ መፍትሄን ይሻል ሲሉ የብራዚል ፕሬዚዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ገለጹ።

ፕሬዚደንቱ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔመክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ፥ እንደ ዓለም ባንክ እና አይ ኤም ኤፍ ያሉ ተቋማት በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚያቀርቡት የብድር አሰራር ተበዳሪ ሀገራትን በሚለውጥ መልኩ መሆን አለበት፡፡

በዚህ ረገድ አፍሪካ በሌሎችም ዓለም አቀፍ ተቋማት ያላት ውክልና ጫና ውስጥ የከተታት መሆኑን ነው ያስረዱት

54 ሀገራትን የያዘች አህጉር የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ አፋጣኝ ጥረቶች ያስፈልጋሉ ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

በዚህ ረገድ ተመሳሳይ ችግሮችን እየተጋፈጥን ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ ፥ ነፃና ገለልተኛ የሆኑ ዓለም አቀፍ ተቋማትን ከመፍጠር አንፃር ብራዚል ከአፍሪካውያን ጎን እንደምትቆም አረጋግጠዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!