የሀገር ውስጥ ዜና

ሞሪታኒያ የ2024 አፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከኮሞሮስ ተረከበች

By Meseret Awoke

February 17, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞሪታንያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦልድ ጋውዛኒ የ2024 የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡

37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤውም ሞሪታኒያ የሊቀመንበርነትን ቦታ የተረከበች ሲሆን ፥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ኦልድ ጋዙዋኒ በ2024 የአፍሪካ ሕብረትን በሊቀ መንበርነት ይመራሉ።

ትምህርት የሁለንተናዊ እድገት መሰረት መሆኑን በመድረኩ ባደረጉት ንግግር የገለፁት ፕሬዚዳንት ሙሃመድ ኡልድ ጋዙዋኒ ፥ የተማረ ሃይል የአህጉሪቱን ፈታኝ ችግሮች ለመቅረፍ ያስችለናል ብለዋል።

ለዚህም ያለውን ሃብት ለትምህርት መሰረተ ልማት ዝርጋታና መሰል ስራዎች ላይ ማዋል እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

በተጨማሪም በአህጉሪቱ የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመከላከል ወጣቱን ኃይል ወደትምህርትና ምርምር ማሰማራት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

ባለፈው ዓመት የኮሞሮስ ፕሬዚዳንት አዛሊ አሱማኒ የሕብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል።

በአሸናፊ ሽብሩ እና ሳሙኤል ወርቃየሁ

#Ethiopia #AU #Mauritania

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!