የሀገር ውስጥ ዜና

የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይጀመራል

By Melaku Gedif

February 17, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ይጀመራል፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ ሰዓዳ አብዱረህማን÷ ጨፌ ኦሮሚያ 6ኛ የሥራ ዘመን 3ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

በጉባዔው የአስፈጻሚ አካላት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ነው የገለጹት፡፡

ጨፌው በመንግስት በጀት አጠቃቀም፣ በልማት ሥራዎች ክትትልና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ እንደሚመክርም ጠቅሰዋል፡፡

ረቂቅ አዋጆች እና ደንቦችን ጨምሮ የተለያዩ ሹመቶች ለጨፌው ቀርበው ይጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting/ ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!