አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳማዊ እመቤቶች ጋር በመሆን በወዳጅነት ፓርክ ሴቶችን ብቻ ተሳታፊ ያደረገውን አውደ ርዕይ መጎብኘታቸውን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ገለጹ፡፡
ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ሴቶች ኢኮኖሚያቸውን በማሳደግ ገቢ ሲያገኙ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ብለዋል፡፡
በኢፌዴሪ ቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀውን አውደ ርዕይም እንድትጎበኙ፤ ሴቶችንም እንድታበረታቱ እጋብዛለሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡