የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከዩ ኤን ዲ ፒ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት አስተዳዳሪና የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

February 18, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዩ ኤን ዲ ፒ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት አስተዳዳሪ እና የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይታቸውም÷ አፍሪካ ለዕድገት ልትጠቀምባቸው ስለምትችለው የወጣቶች ፈጠራ፣ የሥራ ፈጠራ ብሎም የቴክኖሎጂ እርምጃዎች ላይ ማተኮሩን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡