የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ማዳጋስካር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መከሩ

By Feven Bishaw

February 18, 2024

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና ማዳጋስካር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በዛሬው ዕለት በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዳጋስካር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ራሳታ ራፋራቫቪፊካ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ሀገራቱ በግብርና፣ በቆዳ ውጤቶች እና በቱሪዝም ዘርፍ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይትም አካሂደዋል።

በመራኦል ከድር