አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ሂደት በመፋጠን ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ገለጸ፡፡
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ እንዳለ አሰፋ÷ በኢትዮጵያ በርካታ አካባቢዎች የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
ከነዚህ መካከል በ926 ሚሊየን ብር ወጪ እየተከናወነ የሚገኘው የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ አንዱ መሆኑን ተናግረው፤ የግንባታ ሒደቱ 54 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች እየተገነቡ ያሉ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታዎችን የተለያዩ ተቋማትና አካላት እንሚያሰሯቸውና እንደሚከታተሏቸውም ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል የወላይታ ሶዶ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማካሄድ የሳይት ርክክብ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በየሻምበል ምሕረት