አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ37ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ የተሳተፉ መሪዎች እና የልዑካን ቡድን አባላት ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።
ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባዔ ላይ 49 ሀገራት ተሳትፈዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 30 የሀገራት ፕሬዚዳንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮች እንዲሁም ስድስት ምክትል ፕሬዚዳቶች እንደሚገኙበት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።