የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ቼክ ሪፐብሊክ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገለጹ

By Mikias Ayele

February 19, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቁ፡፡

የኢፌዲሪ መንግስት ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደርና ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት አምባሳደር ፍቃዱ በየነ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለቼክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፒተር ፓቬል አቅርበዋል፡፡

አምባሳደር ፍቃዱ÷ በአምባሳደርነት ቆይታቸው በሀገራቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ለዚህም ከቼክ ወገን አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግላቸው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

የቼክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፒተር ፓቬል በበኩላቸው÷ አዲስ የተሾሙት አምባሳደር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ለሚያደርጉት ጥረት መንግስታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እና ትብብር እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ፍቃዱ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ፕሬዚዳንቱ መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን ከጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡