የሀገር ውስጥ ዜና

36ኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

February 19, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና የኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ፍስሃ ሻውል፥ኮሚሽኑ የሀገራቱን የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮችን ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የሁለቱን ሀገራት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ሚና መጫዎቱን አውስተዋል።

በሀገራቱ ድንበር አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮችን በአንክሮ በመለየት የጋራ መፍትሄ በማፈላለግ ረገድ ኮሚሽኑ ትልቅ ስራ መስራት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡

የኬንያ የልዑካን ቡድን መሪ ሞኢ ሊሞሺራ በበኩላቸው ፥ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን የሁለቱን ሀገራት የረዥም ዘመን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል ።

የኮሚሽኑ ስብሰባ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ሦስት ቀናት እንደሚመክር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia #Kenya

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!