የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ቻይና እና ዩኒዶ ለኢትዮጵያ ልማት ላላቸው አጋርነት አመሰገኑ

By ዮሐንስ ደርበው

February 19, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቻይና መንግሥት እና የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) በኢትዮጵያ የዜጎችን ኑሮ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ ላሳዩት ተነሳሽነትና ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በፈጠራ የታገዙ መፍትሄዎችን ለማስገኘት የሦስትዮሽ ትብብር ይፋ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡

ይፋ የተደረገው የሦስትዮሽ ትብብርም÷ በኢትዮጵያ በግብርና፣ በአግሮ ኢንዱስትሪ፣ በታዳሽ ኃይል፣ በዲጂታይዜሽን የልኅቀት ማዕከላትን የመመስረት ሥራ የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን እና የገጠር ነዋሪዎችን ሕይወት ለማሻሻል ልዩ ዕድል ይዞ መጥቷል ብለዋል።

በዚህም የቻይና መንግሥት እና ዩኒዶ በዚህ እጅግ አስፈላጊ ሐሳብ ላይ በመተባበራቸው አመሠግናለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

በተለይም የዩኒዶ ዳይሬክተር ጀነራል ገርድ ሙለር ለኢትዮጵያ የልማት ሥራ ላላቸው የፀና ድጋፍ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው፡፡