አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል በአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ላይ የሚሳተፉ ተወካዮችን ከዛሬ ጀምሮ ከየማኅበረሰቡ እንዲመረጡ እያደረገ ነው፡፡
በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የተወካዮች መረጣም 600 የሚጠጉ ከምሥራቅ ሸዋ ዞን ሊበን ጩቃላ፣ ሉሜ፣ ሞጆ፣ ፈንታሌ፣ ቦራ፣ ቦሰት እና አደአ ወረዳዎች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡
ተሳታፊዎች ስለሀገራዊ ምክክር እና ተያያዥ ጉዳዮች ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚረዱ ገለጻዎች ተደርገዋል፡፡
ለአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ይወክሉናል የሚሏቸውን ሁለት ሁለት ግለሰቦችን ከአንድ ተጠባባቂ ጋር በየወረዳቸው እና በየማኅበረሰብ ክፍሎቻቸው ይመርጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
በተመሳሳይ በነገው ዕለትም የአቃቂ፣ አዳማ፣ ጊምቢቹ፣ የአዳሚ ቱሉ ወረዳዎችን እና በአዳማ ከተማ አሥተዳደር ሥር የሚገኙ ክፍለ ከተሞችን ያካተተ መርሐ-ግብር እንደሚካሄድ ተጠቁሟል፡፡