የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሉ የበልግ ስራ የአመራር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

February 21, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሲዳማ ክልል ”የኩታ ገጠም እርሻ በማስፋት የቤተሰብ ብልጽግና እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል የበልግ ስራ የአመራር የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ እንደገለፁት÷ በክልሉ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የህዝባችንን ህይወት ለመቀየር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

ለዚህም በክልሉ የበልግ እርሻ ስራ በተቀናጀ መልኩ ተጠናክሮ እየተሰራ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡