የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ኬንያ በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ

By Melaku Gedif

February 21, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ኬንያ ፖለቲካና ደህንነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ እና የኬንያ የውጭ ጉዳይ እና የዳያስፖራ ጉዳዮች የካቢኔ ፀሐፊ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ በፖለቲካ እና ደህንነት፣ በቱሪዝም፣ በባህል፣ በ”ብሉ ኢኮኖሚ”፣ በግብርናና ዓሣ ሃብት፣ በዱር እንስሳት ጥበቃ፣ በፐብሊክ ሰርቪስና አቅም ግንባታ ጉዳዮች ሀገራቱን በጋራ መስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

በስምምነቱ ላይ ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር በተለያዩ መስኮች ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ተገልጿል።