የሀገር ውስጥ ዜና

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

By Meseret Awoke

February 25, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ627 በላይ ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በጤናና ሕክምና ሣይንስ ትምህርቶች እንዲሁም በሌሎች የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በማስተርስ፣ በዶክትሬትና በጤና ሰብ ስፔሻሊቲ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው እያስመቀረ ሚገኘው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር አየለ ተሾመን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች በጤናና ሌሎች የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 386 ተማሪዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ አስመርቋል።

የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በምረቃ ሥነ-ሥርዓ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ተመራቂዎች ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመጠበቅ የኅብረተሰቡን የጤና ችግሮች በመፍታት የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ ከዳር ለማድረስ መትጋት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ዕውቀትን በስኬት መደምደም የሚቻለው ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ የማፍራትን ሀገራዊ ተልዕኮ ማሳካት ሲቻል መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በቲያ ኑሬ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!