የሀገር ውስጥ ዜና

በዱከም በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ

By Melaku Gedif

February 26, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ ዱከም ክፍለ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው አንድ ሲኖትራክ፣ ሁለት ሚኒባሶች እና አንድ ላንድ ክሮዘር ተሽከርካሪ እርስ በርስ በመጋጨታቸው ነው የተከሰተው፡፡

በተከሰተው አደጋም የሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ነው የቢሾፍቱ ከተማ ኮሙኒኬሽን መረጃ የሚያመላክተው፡፡

በተጨማሪም 11 ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በቢሾፍቱ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡