አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት 5 ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት ‘አዲስ ወግ’ በሚል በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲካሄድ የቆየው የውይይት መድረክ በመጽሐፍ ተሰንዶ ለንባብ በቅቷል።
በመድረኩ በአደባባይ የሚንጸባረቁ ሃሳቦችን ወደ መድረክ በማምጣት ሀገራዊ ፋይዳቸው ከፍ ያሉ ሃሳቦች የተገኙበት መድረክ እንደነበር ተገልጿል።
በመድረኩ የተደረጉ ውይይቶችም ለመንግስት የፖሊሲ ማውጣት ትልቅ ግብዓት የሆኑበት እንደነበርም ነው የተመላከተው።
መጀመሪያ ላይ የአንድ ዓመት የለውጥ ጉዞን ለመቃኘት ታስቦ የተዘጋጀው አዲስ ወግ ቀጣይነቱ አስፈላጊ ሆኖ ’’አዲስ ወግ አንድ ጉዳይ’’ በሚል ወርሃዊ መድረክ መካሄዱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም ’’አዲስ ወግ ዐቢይ ጉዳይ’’ በሚል የሩብ ዓመት መድረክ ተዘጋጅቶ ትልልቅ ሀገራዊ ጉዳዮች ውይይት መካሄዱንም ነው የገለጹት፡፡
በዚህ የውይይት መድረክ ላይ የተነሱ ሃሳቦችም በመጽሐፍ ተሰንደው ለንባብ መዘጋጀቱንም አንስተዋል።
የ‘‘አዲስ ወግ’’ ውይይት የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በቀጣይ በሌላ ይዘት ‘‘ቅኝት’’ በሚል ይቀጥላልም ነው የተባለው።
#Ethiopia #PMOEthiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!