የሀገር ውስጥ ዜና

ኮርፖሬሽኑ ከዓለም ባንክ ጋር የሚያከናውናቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ

By Meseret Awoke

February 28, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ተቋማዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከዓለም ባንክ ጋር እያከናወናቸው የሚገኙ የጋራ ተግባራትን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከዓለም ባንክ የስራ ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷ በጋራ የሚሰሩ ጉዳዮች ላይ በትብብር እና በመተጋገዝ መንፈስ ለመስራት እንዲሁም እንደ ፕሮጀክትና እንደ ሀገር የሚጠበቁ የጋራ ውጤቶችን በሚፈለገው ጊዜ ለማጠናቀቅ ብሎም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በመድረኩ መነሳቱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመልክቷል።