የሀገር ውስጥ ዜና

አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን ተገላገለች

By ዮሐንስ ደርበው

February 28, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤንች ሸኮ ዞን ኮሰኮል ቀበሌ ነዋሪ የሆነች አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ሕጻናትን ተገላገለች፡፡ ከአራቱ ሦስቱ ወንዶች መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ሕጻናቱ በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል የእናቶችና ጨቅላ ሕጻናት ሕክምና ክፍል ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡

እያንዳንዳቸውም ከ1 ነጥብ 3 እስከ 1 ነጥብ 7 ኪሎ ግራም እንደሚመዝኑ ተጠቅሷል፡፡