የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

June 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጄምስ ሞርጋን ጋር ተወያዩ።

አምባሳደር ጄምስ ሞርጋን በውይይቱ ወቅት ደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም በሚጎዳ በማንኛውም ጉዳይ ላይ እጇን እንደማታስገባ ገልጸዋል።