አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ለሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ የመሠረት ድንጋይ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ እና በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተቀመጠ።
የትምህርት ቤቱ ግንባታ በሰዎች ለሰዎች ግብረሰናይ ድርጅት አማካኝነት የሚካሄድ ሲሆን÷ በአመት አንድ ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ተገልጿል።
በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ የትምህርት ቤቱ ግንባታ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ የጎላ አስተዋፆ እንደሚያበረክት ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት አካል ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የሚገነባው የጅግጅጋ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።