አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማዕድን ምርት ሥራን በቴክኖሎጂ ታግዞ ውጤታማ ለማድረግ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር) ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
አቶ አሻድሊ ሀሰን÷ ክልሉ በግብርናው ዘርፍ፣ በማዕድን ዘርፍና ሌሎች የኢንቨስትመት አማራጮች ሰፋፊ ፀጋዎችን የታደለ መሆኑን አውስተዋል፡፡
በክልሉ ያለውን ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ለመጠቀም ከባህላዊ አመራረት ተላቆ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያጎለብት በቴክኖሎጂ የታገዘ ሥራ ለመስራት በማሽነሪ አቅርቦት ባንኩ እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡
በክልሉ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የታለመላቸውን ግብ ያሳኩ ዘንድ በብድር አቅርቦት አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ከባንኩ እንደሚጠብቁም ጠቅሰዋል፡፡
ዮሃንስ አያሌው (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ ባንኩ እና ክልሉ ግንኙነታቸውን አጠናክረው ከሰሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ክልሉን የኢንቨስትመንት ማዕከል ማድረግ ይቻላል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የክልሉን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማገዝ ይቻል ዘንድ ኢንቨስተሮች ከባንኩ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተ