የሀገር ውስጥ ዜና

በትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

By ዮሐንስ ደርበው

March 04, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከጎንደር ወደ ሑመራ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ በተባለ አካባቢ ባጋጠመ አደጋ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሑመራ ዲስትሪክት ሠራተኛ የሆኑ ሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በአራት የተቋሙ ሠራተኞች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡

የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡