አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2016 የሁለተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀምንመገምገም ጀምሯል።
ግምገማው አራቱን የአስተዳደርና ፍትህ፣ የማኅበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊ ዘርፎችን በተመለከተ በቀረቡ አፈፃፀሞች ላይ ትኩረት በማድረግ መጀመሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሰል የግምገማ መድረኮች በመንግሥት ተቋማት የመፈፀም ባህልን ለማዳበር የጀመሯቸው መሆናቸው ይታወሳል።