የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይና ጉባኤ ተከፈተ

By Shambel Mihret

March 07, 2024

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው ኢትዮ ኸልዝ አውደ ርዕይ እና ጉባኤ በአዲስ አበባ ተከፍቷል፡፡

በአውደ ርዕይ እና ጉባኤው መክፈቻ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ፣ ከፍተኛ የዘርፉ የስራ ሃላፊዎች፣ አምባሳደሮች፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

መርሐ ግብሩ ከየካቲት 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን÷ የአልጀሪያ ብሔራዊ ተሳትፎን ጨምሮ ከ12 ሀገራት የመጡ ከ90 በላይ ኩባንያዎች ተሳትፈዋል፡፡

በአውደ ርዕዩ ከ22 የሙያና የዘርፍ ማህበራት ጋር በመተባበር የሙያ ማጎልበቻ ሥልጠና እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በአውደ ርዕዩና በጉባኤው ላይ የጤና ባለሙያዎችና የዘርፉ የንግድ ባለድርሻ አካላት ከዓለም ዓቀፍ የዘርፉ መሪዎችና ታዋቂ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች ጋር ጠንካራ የንግድ ትስስር እንደሚፈጥሩም ይጠበቃል፡፡

በሃይማኖት ወንድራድ