አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሴን ጋር ተወያዩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስሰር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ የዴንማርክን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሴን እንኳን ወደ ኢትዮጵያ በደህና መጡ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያና ዴንማርክ ለቀጣይ ስራቸው ጠንካራ መሰረት የሚጥል የረጅም ጊዜ አጋር ሀገራት መሆናቸውንም አንስተዋል፡፡
ውይይቱም በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ውጤታማ እንደነበርም ነው የገለጹት።
#Ethiopia #Denmark
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!