የሀገር ውስጥ ዜና

የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

By Shambel Mihret

March 10, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የዲጂታላይዜሽን ስርዓት ለተገልጋዮች ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ የከተማዋ ውስን ሃብት የሆነውን መሬትን በዘመናዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማስተዳደር በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ እየተሰራ ያለውን የዲጂታላይዜሽን እና የሪፎርም ስራ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

በዘርፉ ያለውን የባለ ጉዳይ እንግልት እና ብልሹ አሰራርን የሚያስቀር እንዲሁም ለተገልጋዮች ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል የዲጂታላይዜሽን ስርዓት አበልፅገን ለአገልግሎት ዝግጁ አድርገናልም ነው ያሉት፡፡

የዲጂታላይዜሽን ስራው ከማዕከል እስከ ክፍለ ከተሞች ያለውን መሬት በአንድ ማዕከል ለማስተዳደ አቅም እንደሚፈጥርም ጠቅሰዋል፡፡

ሲስትሙ በየደረጃው ያለውን አገልግሎት ክትትል ለማድረግ እና ለተገልጋዮች ፍትሃዊ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ይሆናል ብለዋል፡፡