አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የተሾሙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋል።
የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ያቀረቡት የማሊ፣ ህንድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኬፕቨርዴ፣ ቦትስዋና እና ጃማይካ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ናቸው።
ተሿሚ አምባሳደሮቹ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡