የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ እንዳሻው ጣሰው ሠላምን ለማፅናት ዘብ መቆም እንደሚገባ አስገነዘቡ

By ዮሐንስ ደርበው

March 17, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር እንዳሻው ጣሰው የሁላችንም ጉዳይ የሆነውን ሠላምን ለማፅናት ዘብ መቆም አለብን ሲሉ አስገነዘቡ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሠላም ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የሁላችንም ጉዳይ የሆነውን ሠላምን ለማፅናትም ዘብ መቆም አለብን ነው ያሉት፡፡

በሠላም መደፍረስና በግጭት ጥቂቶች ጊዜያዊ ጥቅም ያገኙ ሊመስላቸው እንደሚችል ጠቁመው÷ ነገር ግን ሠላም ለዘላቂ የጋራ ዕጣፈንታችን መልካም መሆን እጅግ መሠረታዊ እሴት ነው ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ለሠላም ግንባታና ለሠላም እሴቶች መጠናከር በጋራ በመሥራት ኃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል ብለዋል በመልዕክታቸው፡፡