የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተዘጋጀ የፀሎት መርሃ ግብር ተካሄደ

By Feven Bishaw

March 17, 2024

 

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የተዘጋጀ የፀሎት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡

 

ለሀገር ሰላምና አንድነት  እየተካሄደ በሚገኘው የጸሎትና ምስጋና መርሃ ግብር በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ስር ያሉ የተለያዩ ቤተክርስቲያናት መሪዎች፣ አባቶች፣ ዘማሪያን፣ መጋቢዎች እና ሌሎችም ተገኝተዋል።