የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አሻድሊ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

March 22, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በወቅታዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ፡፡

በውይይታቸውም በሕዝቡ ሠላም እና ደኅንነት ብሎም በልማትና በምርጫ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አቶ አሻድሊ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር ባደረግነው ምክክር መሠረትም የቀጣይ አቅጣጫዎች አስቀምጠናል ነው ያሉት፡፡