የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ አረጋ ከበደ የአባይ ሲሚንቶ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማሕበር የሥራ አፈጻጸምን ገመገሙ

By Shambel Mihret

March 23, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድ አረጋ ከበደ የአባይ ሲሚንቶ ኢንዱስትሪያል አክሲዮን ማሕበር የሥራ አፈጻጸምን ገምግመዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ አክሲዮን ማህበሩ እስከ አሁን ያለውን የሥራ አፈፃፀም በመገምገም የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በመድረኩ የክልሉ ማዕድን ሐብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃይሌ አበበ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኑርልኝ ብርሃኑ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት መኘታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡