አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል::
በጉብኙቱ ወቅት ተማሪዎቹ የዓድዋ ድል መታሰቢያን በመጎብኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
በመንግስት የተሰራው ስራ እነሱም ወደፊት ለሀገራቸው በጎ እና ለትውልድ የሚተላለፍ ታሪክ ሰርተው እንዲያልፉ እንዳነሳሳቸው መናገራቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡