👉 ችግሩ በተከሰተበት ዕለት ከምሽቱ 3፡38 ጀምሮ እስከ ሌሊቱ 8፡45 ድረስ በ25 ሺህ 761 ሂሳቦች አማካኝነት 238 ሺህ 293 ሕገ-ወጥ ግብይቶች ተከናውነዋል፣
👉 ባንኩ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት ላይ ባጋጠመው ችግር ምክንያት ያለአላግባብ ከተወሰደበት 801 ሚሊየን 417 ሺህ 747 ብር ከ81 ሣንቲም ውስጥ 622 ሚሊየን 900 ሺህ ብር (78 በመቶው) እስካሁን ተመልሷል፣
👉 168 ሚሊየን 609 ሺህ 283 ብር ከ7 ሣንቲም ለመመለስ ቃል ተገብቷል፣
👉 ችግሩ መከሰቱ ከታወቀ በኋላ የባንኩን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ ለተወሰኑ ሰዓታት በማቆም እና ችግሩ በተከሰተበት ሰዓት በገንዘብ ዝውውር የተሳተፉ ሂሳቦችን በማገድ የጉዳት መጠኑን መቀነስ ተችሏል፣
👉 ባንኩ በወሰዳቸው እርምጃዎች ያላግባብ የገንዘብ እንቅስቃሴ ከተደረገባቸው እና በቂ ገንዘብ ከነበራቸው ከ10 ሺህ 727 ሂሳቦች ቀጥታ ብር 44 ሚሊየን 668 ሺህ 232 መቶ ብር ከ41 ሣንቲም ተመላሽ ተደርጓል፣
👉 ከ15 ሺህ 8 ሂሳቦች ደግሞ በከፊል ማለትም 205 ሚሊየን 805 ሺህ 340 ብር ከ9 ሣንቲም ተመላሽ ተደርጓል፣
👉 በጉዳዩ ተሳትፎ የነበራቸው 9 ሺህ 281 ግለሰቦች የወሰዱትን 223 ሚሊየን 475 ሺህ 369 ብር ከ31 ሣንቲም ሙሉ በሙሉ በፈቃደኝነት መልሰዋል፣
👉 5 ሺህ 160 ደንበኞች ደግሞ በከፊል ማለትም ብር 149 ሚሊየን 21 ሺህ 191 ብር ከ37 ሣንቲም መልሰዋል፣
👉 ያለግባብ ከወሰዱት 9 ሚሊየን 838 ሺህ 329 ብር ከ12 ሣንቲም እስካሁን ምንም ያልመለሱ 567 ግለሰቦች የወሰዱትን ገንዘብ ለማስመለስ ባንኩ ወደቀጣይ እርምጃዎች የሚገባ ይሆናል፣
👉 ገንዘቡን ያልመለሱት ግለሰቦች ይታወቃሉ፣
👉 ከተወሰደው ገንዘብ ውስጥ አንድ ግለሰብ የወሰደው ከፍተኛው ብር 304 ሺህ ብር ነው፣
👉 ከአምስት ብር በታች የወሰዱም አሉ፣
👉 ባንኩ በቀጣይ ገንዘቡን የወሰዱ ግለሰቦችን የስም ዝርዝር ሂሳባቸው ባለበት ዲስትሪክት እና ቅርንጫፍ እንዲሁም በባንኩ ማኅበራዊ ሚዲያ በመለጠፍ እስከ ፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንዲመልሱ ያደርጋል፣
👉 ከላይ እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ገንዘቡን በማይመልሱ ግለሰቦች ላይ ጉዳዩን እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የመውሰድ እርምጃ ይወሰዳል፡፡