አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ብልፅግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል የተለዩ ችግሮችን በመፍታት ለሀገራዊ ሰላምና ለህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እንደሚሰራ በፓርቲው የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ፓርቲው ከህዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን የሚመጥን የተግባር ምላሽ ለመስጠት ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ነው ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) የተናገሩት፡፡
ፓርቲው በህዝብ ይሁንታ ምርጫ አሸንፎ መንግስት ከመሰረተ ወዲህ ድሎችን ማስመዝገቡን በመግለጽ መልስ የሚሹ የህዝብ ጥያቄዎችም መኖራቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የሰላም ችግሮች፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የኑሮ ውድነትና የስራ አጥነትን ጨምሮ ሰባት መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮችም በህዝባዊ ውይይቶች መለየታቸውን አንስተዋል።
ፓርቲው በክልሉ ህዝብ የተለዩ ችግሮችን በመፍታት ለሀገራዊ ሰላምና ለህብረብሔራዊ ወንድማማችነት ይሰራልም ብለዋል።
በአፈወርቅ እያዩ