የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ፑንትላንድ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

By Mikias Ayele

April 03, 2024

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ፑንትላንድ ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ለማሻሻል መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በፑንትላንድ የገንዘብ ሚኒስቴር ሞሃመድ ፋራህ ሞሀመድ ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ አምባሳደር ምስጋኑ የፑንትላንድ መንግስት በቅርቡ ያካሄደውን ሰላማዊ ምርጫ አድንቀው÷ ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላትን ዘርፍ ብዙ ትብብሮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

የፑንትላንድ ልዑክ በበኩሉ÷ ኢትዮጵያ እና ፑንትላንድ የቆየ የወንድማማችነት ግንኙነት እንዳላቸው አንስቷል፡፡

ኢትዮጵያ በፑንትላንድ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን የገለፀው ልዑኩ÷ በፑንትላንድ አዲስ የተመረጠው መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት የማሳደግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

በውይይቲ በኢትዮጵያ እና በፑንትላንድ መካከል በንግድ፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና በሌሎች የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚያስፈልግ መገለፁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡